በኢትዮጵያ የበይነመረብ ተጠቃሚዎች በኢንተርኔት ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን አመለካከት የተመለከተ ጥናት ተደረገ፡፡

98 ከመቶ የበይነመረብ ተጠቃሚዎች የኢንተርኔት ደህንነት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የበይነመረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት መስጠት ከተጀመረ አስር ዓመት በላይ አልፎታል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የተጠቃሚዎቹ አሃዝ አናሳ ነበር፡፡ በ2000 ዓም የበይነመረብ ተደራሽነቱ 0.4 በመቶ ብቻ የነበር ሲሆን በ2009 ዓም ግን ተደራሽነቱ ወደ 15.4 በመቶ ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ እንዳላት […]

Read More

አቶ ማሙሸት አማረ የተመሰረተባቸውን የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተከላከሉ ተብለዋል፡፡

የመኢአድ የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን የሽርተኝነት ወንጀል ክስ ይከላከሉ ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 19/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት በይኗል፡፡ ፍ/ቤቱ መዝገቡን ለዛሬ ቀጥሮ የነበረው የአቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ ብይን ለመስጠት ሲሆን፣ በዚህም ተከሳሹ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የቀረበባቸውን […]

Read More

የመንግስቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማረሚያ ቤት የደረሰውን የመብት ጥሰት አስመልክቶ ያቀረበው ሪፓርት

የቅሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ ማስረሻ ሰጠ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደረሰብን ብለን አቤቱታ ሲያቀርቡ መክረማቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የመንግስቱ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣሪያ እንዲያደርግ ባዘዘው መሰረት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሚከተለውን ሪፓርት ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡ (ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ ) እነ ማስረሻ ሰጤ (ሰብአዊ መብት) 

Read More

የእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ በተያዘው ቀጠሮ ምስክሮች ሰይደመጡ ቀሩ። (ጥቅምት 28 ፣2010)

* ችሎቱ ምስክሮች በተከሳሾች እና ዳኞች አለመግባባት ተቋርጧል። የእነ ጉርሜሳ አያኖን መዝገብ ለዛሬ ጥቅምት 28 ፣ 2010 የተቀጠረው ከአንደኛ እሰከ አራተኛ ካሉት ተከሳሾች ውጪ ያሉ ተከሳሾችን መከላከያ ምስክሮች ለመስማት በሚል ነው። በጠዋቱ ችሎት ዳኞች ሌሎች መዝገቦችን ሲሰሩ ስለነበር ቀጠሮው ወደ ከሰአት ዞሯል። ተከሳሾቹ የሚመገቡትን ምሳ በተመለከተ ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ዳኞቹን ለማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ትእዛዝ […]

Read More

በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ለመከላከያ መስክርነት የተጠሩ ባለስልጣናት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡ (ጥቅምት 27፣ 2010)

“ለምስክርነት የተዘረዘሩት ባለ ስልጣናት መጥሪያ አልተላከላቸውም፡፡” ፍርድ ቤቱ “ከተከበሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር አንድ ላይ የምክር ቤት አባል ነበርን፡፡ እሳቸው ኢህአዴግ ስለሆኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ እኔ ተቃዋሚ ስለሆንኩ እስር ቤት ገባሁ፡፡” ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጣፋ  “እኔ በተሰጠው ቀጥሮ (ህዳር 6) ልቀርብ ፈቃደኛ አይደለሁም፡፡ ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎች አሉ ማለት ነው? በፍርድ ቤቱ አካሄድ   አላመንኩበትም፡፡” […]

Read More