‹‹በተደጋጋሚ ድብደባ ተፈጽሞብኛል›› ትዕዛዙ ወልዴ

ስም፡- ትዕዛዝ ወልዴ አንቡሌ

ዕድሜ፡- 30

አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08

አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡– ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡– የሰንደቅ ዓላማ አዋጅን በመጣስ አርማ የሌለው ሰንደቅ አላማ ይዞ መገኘት የሚል ነው፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡– በቀን 22/06/09 ምሽት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጎተራ ኦይል ሊቪያ ፊት ለፊት በህግ የተከለከለውንና አርማ የሌለውን ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የሆነውን በመሃሉ ያለምንም አርማ ይዞ ሲሄድ የተያዘ በመሆኑ አርማ የሌለው ሰንደቅ አላማ መጠቀም ነው የተከሰስኩት፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡

  1. በተደጋጋሚ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
  2. ጠያቂ ተከልክዬ ለቀናት ቆይቻለሁ፡፡
  3. ለወራት ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ኮማንድ ፖስት ነው ያሰረህ በሚል ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡
  4. ከወራት እስር በኋላ ፍ/ቤት ስቀርብም የተከሰስሁበት ህግ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም ዋስትና ተነፍጎኝ በእስር እንድቆይ ተደርጌያለሁ፡፡
  5. በምከተለው የፕሮቴስታንት ሐይማኖት መነሻነት ተሰድቤያለሁ፡፡
  6. ማስፈራሪያና ዛቻ በመርማሪዎቼ በተደጋጋሚ ደርሶብኛል፡፡

የኋላ ታሪክ:

ከ23/06/09 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እገኛለሁ፡፡ ተወልጄ ያደግሁት ሀረር ሲሆን ትምህርቴንም እዚያው ሀረር ተምሬያለሁ፡፡ የታሪክ አስተማሪ ሆኜ ስሰራ በነበርሁበት ጊዜ በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ከስራዬ ተባርሬያለሁ፡፡ አዲስ አበባ ዘመድ ለመጠየቅና ስራ ፍለጋ በሚል በመጣሁበት ነው ለእስር የተዳረግሁት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *