ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ለመስጠት በሚል ቀጠሮ ተሰጠበት (ሚያዝያ 20/2009 )

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው በተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት ማስረጃዎችን ሰምቶ ያጠናቀቀው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በመዝገቡ ላይ የፍርድ ውሳኔ ለማሳለፍ በሚል ብቻ ለ3ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍ/ቤቱ ለዛሬ ሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም ፍርድ ለማሰማት በሚል ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ‹‹ተከሳሹ የካቲት 30/2009 ዓ.ም በችሎት የሰጠው የተከሳሽነት መከላከያ […]

Read More

ዶ/ር መረራ ጉዲና በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ አስገቡ (ሚያዚያ 16/2009)

በመረራ ጉዲና መዝገብ ለሚያዝያ 16/2009 የተቀጠረው በክሱ ተካተው በሃገር ውስጥ የሌሉ ግለሰቦች እና ሚዲያዎች ጉዳያቸው በሌሉበት እንደሚታይ ከተወሰነ በኋላ፤ 1ኛ ተከሳሽ የሆኑት ዶ/ር መረራ በቀረበባቸው ክሶች ላይ ያላቸውን መቃወሚያ ለመስማት ነው። በዚህ መሰረት ዶ/ር መረራ በጠበቆቻቸው አማካኝነት 11 ገፅ የመቃወሚያ አቅርበዋል። በፅሁፍ የቀረበው መቃወሚያን በችሎት መሰማቱ አስፈላጊ እንዳልሆነ ዳኞች የተናገሩ ቢሆንም፤ ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ችሎቱ […]

Read More

የአቶ በቀለ ገርባና ሌሎች 22 ተከሳሾች የክስ ሂደት እንዲሁም በቂሊንጦ እስር ቤት ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ

በአስከፊ እስር ውስጥ አልፈው ዳግም ለእስር የተደራጉት የኦሮሞ ፌደራሲስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች 22 ተከሳሾች የክስ ሂደት እንዲሁም በቂሊንጦ እስር ቤት ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ምን ይመስላል የሚለውን የዋዜማ ራዲዮ ባልደረባ ኤዶም ካሳዬ ከአዲስ ስታንዳርድ ኦንላይን ሚድያ ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ እና ከሰብአዊ መብት ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ሶልያና ሽመልስ የተደረገውን ውይይት ያድምጡ።

Read More

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ዋስትና ተከለከለ::

ከሽብርተኝነት ክስ ነጻ ተብሎ በመደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንዲከላከል ብይን የተሰጠው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 13/2009 ዓ.ም ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ከቀረበበት የሽብር ክስ ነጻ በማለት ክሱ ወደ መደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ተቀይሮ አንቀጽ 257 (ሀ) ላይ የተመለከተውን እንዲከላከል […]

Read More

በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ቀሪ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠሮ ተሰጠ ( የታህሳስ 20 የፍርድ ቤት ውሎ)

ታህሳስ 20 በዋለው ችሎት 2ት ምስክሮች ተሰምተዋል:: አቃቢ ህግ በ6ኛ (ገላና ነገራ) እና 11ኛ(በየነ ሩዳ) ተከሳሽ ላይ የሚመሰክሩ ምስክሮች እንደቀረቡ ለችሎት አሳውቆ የሚመሰክሩበትን ጭብጥ አሲዟል፡፡ 11 ተከሳሽ በሆነው በየነ ሩዳ ላይ ለመመስከር የቀረቡት አቶ ዳውድ አበጋዝ ሲሆኑ በ20/05/2008ዓም በፌደራል ወንጀል ምርመራ ማእከል ተገኝተው ከተከሳሽ ኢሜል፣ ፌስቡክ እና ሞባይል ላይ መረጃዎች ሲወጡ የታዘቡትን እንደሚመሰክሩለት አቃቢ ህግ […]

Read More