የመሬት መብት ተሟጋቹ ቄስ ኦሞት አግዋ ሁለት መከላከያ ምስክሮቹን አሰማ። (ሰኔ 05/2009)

በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋመቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ኦኬሎ አኳይ የቄስ ኦሞት መከላከያ ሆነው ቀረቡ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ቀን ሰኔ 05/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ኦሞት አግዋን መከላከያ ምስክሮች ሰምቷል። ተከሳሹ በመጋቢት 18/2009ዓም ካሰማቸው 5 የመከላከያ ምስክሮች በተጨማሪ ዛሬ ሁለት መከላከያ ቀርበው ምስክርነታቸው ሰጥተዋል። የተከሳሹ ጠበቃ በእለቱ ከተገኙት ሁለት ምስክሮች በተጨማሪ ከዘዋይና ሸዋ […]

Read More

ዮናታን ተስፋዬ ስድስት አመት ከስድስት ወር ቅጣት ተወሰነበት::

ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ውሎው በሽብር ወንጀል የተጠረጠረው ዮናታን ተስፋዬ ስድስት አመት ከስድስት ወር ቅጣት ወስኖበታል፡፡ ጠበቃ ሽብሩ በለጠ ስድስት የቅጣት ማቅለያዎችን ለፍ/ቤቱ በፅሁፍ ማስገባታቸውን በገለፁበት በዚህ ችሎት ከስድስቱ ቅጣት ማቅለያዎች የበጎ ስራ ስራዎችን በነፃ መስራቱ፣ በበጎ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ ማካሄድ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ብቻ መቀበሉን […]

Read More

በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የአቃቤ ህግ ምስክሮች አልቀረቡም። ( ግንቦት 15/2009)

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ችሎት የሚታየው የእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ  ለዛሬ ግንቦት 15/2009 ቀን የተቀጠረው ቀሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመጠባበቅ ነበር። አቃቤ ህግ ከዘረዘራቸው ምስክሮች በዛሬው ቀጠሮ እንዲቀርቡ ይጠበቁ ከነበሩት 4ቱ ውስጥ 3ቱ ባስመዘገቡት አድራሻ ፓሊስ አፈላልጎ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ቀሪው አንድ ምስክር ደግሞ የቲቢ ህመምተኛ በመሆኑ ታሞ ካልጋ መንቀሳቀስ እንደማይችል ተጠቅሶ ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጥ […]

Read More

እነ ጉርሜሳ አያና ለ5ኛ ጊዜ ብይን ለመስማት ተቀጠሩ (ግንቦት 7/2009)

እነ ጉርሜሳ አያኖ ለዛሬ ግንቦት 7/2009 ተቀጥረው የነበረው አቃቢ ህግ ባቀረበው የሰው፣ የሰነድ እና የድምፅ ከምስል ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን ለማሰማት ነበር። ሆኖም መዝገቡን የሚያዩት የ4ኛ ችሎት ዳኞች መዝገቡን የመመርመር ስራ እንዳላለቀላቸው በመናገር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል።  የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን እንዲተረጉማቸው ከተላኩ የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ውስጥ በ11ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው ተቆርጦ መቅረቱን የተቀሩት ግን ተተርጉመው መቅረባቸውን የገለፁት […]

Read More

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ለመስጠት በሚል ቀጠሮ ተሰጠበት (ሚያዝያ 20/2009 )

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው በተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት ማስረጃዎችን ሰምቶ ያጠናቀቀው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በመዝገቡ ላይ የፍርድ ውሳኔ ለማሳለፍ በሚል ብቻ ለ3ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍ/ቤቱ ለዛሬ ሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም ፍርድ ለማሰማት በሚል ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ‹‹ተከሳሹ የካቲት 30/2009 ዓ.ም በችሎት የሰጠው የተከሳሽነት መከላከያ […]

Read More