ኢሰመፕ በእስረኞች ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት የመሰነድ ፕሮጅክቱን መሰረት አድርጎ የሚከተለውን በአክቲቪስት ንግስት ይርጋን የእስር ቤት ስቃይ በአኒሜሽን ቪዲዮ አዘጋጅቶ አቅርቦላችኋል፡፡ ይመልከቱ! ያጋሩ ! ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ያሳዩ!
ፍትሕ የማግኘት መብት
የዶ/ር መረራ ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትርጉም እንዲሰጥበት ትእዛዝ ተሰጠ – ሠኔ 30 2009

የእነ ዶ/ር መረራ ጉዲና መዝገብ ለዛሬ የተቀጠረው ከዚህ ቀደም በቀረበው መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር። በመሆኑም ዛሬ – ሰኔ 30/2009 – ዶ/ር መረራ ጉዲና በተመሰረተባቸው 3ት ክሶች ላይ ያቀረቧቸው መቃወሚያዎች ላይ 19ኛው ወንጀል ችሎት ከፊል ብይን ሰጥቶበታል። ችሎቱ፣ ዶ/ሩ ያቀረቡትን ክሱ እንዳይንጓተት ከሌሎቹ በሌሉበት ከተከሰሱት ሶስት ተከሳሾች ይነጠልልኝ የሚለውን መቃወሚያ ጨምሮ ሌሎቹን መቃወሚያዎች በሙሉ ውድቅ […]